Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን የላቦራቶሪ ማሽኖችን ለጤና ተቋማት አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በከፍተኛ ወጪ የተገዙ የሲ ቢ ሲ እና ኬሚስትሪ የላቦራቶሪ ማሽኖችን ለወረዳ ጤና ጣቢያዎች እና ጁገል ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በወቅቱ እንዳሉት÷ የጤና ተቋማትን በግብዓት በማደራጀት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ማሽኖቹ ዜጎች የፈለጉትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ በማስቻል በተገልጋዮች ላይ የሚደርሰውን አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት ያስቀራሉ ብለዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ በበኩላቸው÷ ማሽኖቹ ተገልጋይ ይበዛባቸዋል ተብሎ ለተለዩ የወረዳ ጤና ጣቢያዎች እና ጁገል ሆስፒታል መተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡

የተገልጋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ ማሽኖቹ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተወሰነ ደረጃ እንደሚቀርፉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.