Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ለሰላም ግንባታ ስራዎች የ40 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ለሰላም ግንባታ ስራዎች መኪናዎችን ጨምሮ 40 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)÷የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር የሰላም ግንባታ ስራዎችን ታከናውናለች ብለዋል።

በዚህም ሀገሪቱ በጋራ ለመስራት በገባችው ቃል መሰረት ድጋግ መደረጉን ጠቅሰው፤ 40 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የመሐመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሀሊፋ አል ዳህሊን በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በተለይም ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ እና አሁን የተደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.