1 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ወገኖችም ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ71 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተመላክቷል፡፡