ከ28 ሺህ ለሚልቁ ከስደት ተመላሾች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም ለ28 ሺህ 380 ከስደት ተመላሾች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ።
የሥራ ዕድሉ የተፈጠረውም በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር በሙያቸው ጭምር የሚሠሩበት ዕድል በማመቻቸት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 345 ሺህ ሰዎች ስልጠና ወስደው በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ መሄዳቸውን እና በ2017 ዓ.ም ደግሞ ለ700 ሺህ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡