በሐረማያ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በሐረማያ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ፡፡
የኃይል መቋረጡ ዛሬ 5 ሠዓት ከ30 ላይ ማጋጠሙን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት÷ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞቹ አገልግሎቱ ዳግም እስከሚመለስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡