ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ኤልኢዲ አምፖልና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ታገዱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምንጫቸው ያልታወቁ እና ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ኤልኢዲ አምፖል፣ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያና ዋየር ምርቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከገበያ መታገዳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከገበያ ላይ በተወሰደው ናሙና ላይ በተደረገው የ3ኛ ወገን የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት ምርቶቹ የጥራት መስፈርት ያላሟሉና በተደረገው የምርት ዱካ የማጣራት ሥራ መሰረት የአምራቹ ስምና አድራሻ የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ምርቶቹ የሚጠበቀውን የጥራት መስፈርት ያላሟሉ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀም ከገበያ መታገዳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምርቶቹን ሲሽጥ የተገኘ ነጋዴም ሆነ ግለሰብ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድብትም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡