Fana: At a Speed of Life!

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 20 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 20 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከአዲስ አበባ ጅማ በር ቶታል ማደያ 20 ሺህ ሊትር ቤንዚን በሕገ-ወጥ መንገድ በመቅዳት ወደ አሶሳ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ነው በቡራዩ ኬላ የተያዘው፡፡

ነዳጁን በማጓጓዝ ሒደት ውስጥ ሕገ-ወጥ ሠነዶችን በማዘጋጀት ለማጭበርበር የተደረገ ጥረት እንዳለ መረጋገጡን የባለስልጣኑ መረጃ አመልክቷል፡፡

ሕገ-ወጥ ነዳጁ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ መወሰኑም ነው የተጠቆመው፡፡

ባለስልጣኑ ሕጋዊ ሽፋንን በመጠቀም ነዳጅን በጥቁር ገበያ ለመሸጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደማይታገስ አስታውቋል።

ከአሰራር ውጪ ነዳጅ ለአደጋ ተጋለጫ በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ እንዲወጣ ባደረገው ማደያ ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድም ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ ሁኔታ መነሻውን ቢሾፍቱ ከተማ አድርጎ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተገኘ 121 በርሜል ቤኒዚን በቡራዩ ኬላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.