የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት ተዘጋጀ

By Tibebu Kebede

June 22, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት መዘጋጀቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ስፖርት አካዳሚው 300 ቀላል ምልክት የሚያሳዩና ምንም ምልክት የሌላቸው ነገር ግን በቤታቸው ለመቆየት አመቺ ሁኔታ የሌላቸውን ታካሚዎች ለመቀበል ዝግጁ ሆኗል።

ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ ላደረጉት የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ቡድንም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።