አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ እና ኮመንዌልዝ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ፣ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል፡፡
ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅድ መፈጸም ብሪታኒያ ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደር ታዬ፤ በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ተወያይተናል ብለዋል።
በተለይም በድህረ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) እና በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ሰላም እንዲመጣ የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።