Fana: At a Speed of Life!

የሕዝቡን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር የአመራሩ ሚና ሊጠናከር ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ዘላቂ ሰላም በማስፈን የሕዝቡን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሚና እንዲጠናከር የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አለሚቱ ኡሞድ አሳሰቡ፡፡

በክልሉ ሰሞኑን የተሾሙ አዳዲስ አመራሮች ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከተውጣጡ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ በተለያየ ጊዜ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች በሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የልማት ሥራዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል።

በመሆኑም ችግሮቻችንን በጋራ የመፍታት ባህላችንን በማጎልበት ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም ተባብረን መስራት ይኖርብናል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የሪፎርም ስራዎቻችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እንዲፈጸሙ አስገንዝበው÷ በክልሉ ሰላምን በማስፈን ሕዝቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሚና እንዲጠናከር አሳስበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሏክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ አመራሩ በተለየ ሁኔታ በአሁኑ ሰዓት መስራት የሚጠበቅበት ክልሉ ሰላማዊና ልማት ያለበት ሆኖ እንዲቀጥል ማስቻል ይሆናል ብለዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት ቢሆንም ክልሉ ካለው ሀብት አኳያ በርካታ ስራዎችን የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.