Fana: At a Speed of Life!

በፎረሙ የአህጉሪቱ ከተሞች ቀጣይ የዕድገት አቅጣጫ እንደሚመላከት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአጀንዳ 2063 ማዕቀፍ የአህጉሪቱ ከተሞች ቀጣይ የዕድገት አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አመላከቱ፡፡

ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም “ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡

በፎረሙ የበርካታ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንደሚሳተፉ ጠቁመው÷ ፎረሙ የአፍሪካ ከተሞችን ዕድገት የሚያነቃቃና ቀጣይ የዕድገት አቅጣጫ ይመላከትባል ብለዋል፡፡

ፎረሙ ከአህጉሪቱ ከተሞች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቁልፍና ወሳኝ ችግሮች እንዲፈቱና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ምክረ ሐሳቦች የሚመላከቱበት ይሆናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ፎረሙን የማስተናገድ እድል ያገኘችው በሀገሪቱ የከተሞች ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱና ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ መንግሥት ለከተሞች በሰጠው ትኩረት መሠረት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በፎረሙ አጠቃላይ የከተሞች ዕድገት እንዲረጋገጥ ምን መሠራት አለበት? እንዲሁም ማን ምን ማድረግ አለበት? በሚለው ጉዳይ ላይም አቅጣጫ ይቀመጣል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.