ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
የኮሚሽኑ አባላት በሀገሪቱ ብሄራዊ መግባባትን ለማስፈን በሚያከናውኗቸው ተግባራት የከተማ አስተዳደሩ ትብብርና ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል፡፡
ኢንጅነር ታከለ ኡማ ኮሚሽኑ ቁርሾዎችንና ቅራኔዎችን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ዝግጅትና ጥረት አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ ለኮሚሽኑ ሀሳብ ስኬት ድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከክልል መስተዳድር አመራሮችና እና ከከተማ መስተዳድር አመራሮች ጋር ትውወቅና ውይይት እያደረጉ እንደሚገኝ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡