Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ለአቅመ ደካሞች የሚውል የ21 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ለአፋር ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች የሚውል የ21 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ÷ለተቸገሩ እና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረግ ፈጣሪን የሚያስደስት ሥራ ነው ብለዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው÷ሚኒስቴሩ በክልሉ የሚያከናውነውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ማስጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

የእድሳት ሥራው በሁሉም አካላት የቅርብ ክትትል በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ አስገንዝበዋል፡፡

ድጋፍ የተደረጉት ዕቃዎች የኮሚሽኑ ሰራተኞች መስዋዕትነትን በመክፈል ጭምር በኮንትሮባንድ የተያዙ መሆናቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጠቁመዋል፡፡

ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 15 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚሆነው የአይነት ሲሆን÷ 6 ሚሊየኑ ደግሞ በጥሬ ገንዘብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.