Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ በጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነትና ጥብቅ ክትትል በተሳካ መልኩ ተከናውኗል – አቶ ጥራቱ በየነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነትና ጥብቅ ክትትል በተሳካ መልኩ ተከናውኗል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ጥራቱ በየነ ገለጹ።

የኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን ገጽታያስዋበና የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቱ ፍጥነትና ስኬታማነት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ሌት ተቀን እንዲሰራ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸው ጠቅሰው÷የልማቱ ስኬት የአመራሩና አጠቃላይ የነዋሪው የጋራ ትብብር ውጤት ነው ብለዋል።

ለኮሪደር ልማቱ ከጥናት ጀምሮ የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን አስታውሰው÷ የፕሮጀክቱ ክንውንም በተቀመጠለት ጊዜ፣በጥራትና በፍጥነት መከናወኑን ለኢዜ ገልጸዋል።

በክንውን ሂደቱ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት እልባት በመስጠት ረገድ የአመራሩ ቅንጅት፣የነዋሪው ትብብርና የስራ ተቋራጮቹም ጥረት የላቀ መሆኑን አቶ ጥራቱ አንስተዋል።

የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባን ገጽታ ያስዋበና የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠና የብዙዎችን ተሳትፎ ያማከለ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በዚህ ረገድ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የግል ባለሃብቱ፣ ነዋሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለነበራቸው የላቀ ተሳትፎ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የልማት ፕሮጀክቱ የህንጻ ደረጃዎችን፣ የአካባቢ ንጽህናን፣ የአረንጓዴ ልማትን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን፣የወንዝ ዳርቻ ልማትን፣ የፓርኪንግ አገልገሎትና የትራንስፖርት ስቴሽኖችን ያቀናጀና በተናበበ መልኩ የተከናወነ ስለመሆኑም አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.