በኦሮሚያ ክልል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው ችግኝ ተከላ ዝግጅት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ኦሮሚያ ክልል ዝግጅቱን አጠናቀቀ፡፡
በዚሁ መሠረት የመትከያ ሥፍራ፣ የሚተከሉ ችግኞች ዓይነት እና ብዛት ልየታ መጠናቀቁን የገለጹት የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ÷ በዕለቱ ከ21 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አመላክተዋል፡፡
በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 4 ነጥብ 9 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን እና እስከ አሁንም 4 ነጥብ 4 ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በተለያዩ አካባቢዎች የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በፀሐይ ጉልማ