Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተሻለ ምርት ለማግኘት የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ያለውን የእርሻ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ነስረዲን አሕመድ ገለጹ፡፡

በ2016/17 የመኸር ወቅት 8 ሺህ 853 ሔክታር መሬት በማሽላ፣ በቆሎ እና ስንዴ እየለማ መሆኑን የገለጹት አቶ ነስረዲን÷ ከዚህም 210 ሺህ ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የዝናብ እጥረትን በመቋቋም በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጥ 100 ኩንታል “መልካም” የተሰኘ የማሽላ ዝርያ በ800 ሔክታር ላይ በኢንሼቲቭ መዘራቱንና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠላቸው ጠቅሰው÷ በወተት፣ እንቁላል፣ በማር ምርት እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሰፋፊ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ተግባር የግብርና ምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከማስቻሉ በተጨማሪ÷ አምራቹንና ተጠቃሚውን እርስ በርስ በማገናኘት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ አስችሏል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.