Fana: At a Speed of Life!

ክልሎች በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው ችግኝ ተከላ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ዓርብ በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልል የመትከያ ቦታን ጨምሮ የችግኞችን ዓይነትና መጠን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላው ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ኡጁሉ ሉዋል ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ እየተተከሉ ከሚገኙ ችግኞች መካከልም ከ60 በመቶ የሚልቁት የፍራፍሬና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መምህሩ ሞኬ እንዳሉት÷ የፊታችን ዓርብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡

ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ገልጸው÷ በዕለቱ በክልሉ ከሚተከሉ ችግኞች መካከልም 1 ሚሊየን የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ዐሻራችንን እናኑር በማለት መልዕክት ማስላለፋቸውን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.