Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ወረዳ የሚገኙ የተለያዪ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 16 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ሀዋስ ወረዳ የሚገኙ የተለያዪ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

በኦሮሚያ ክልል ግንባታቸው የተጠናቀቁ የተለያዩ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

በዚህም በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ከሁለት አመት በላይ ግንባታቸው የዘገየ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ሁለት ወረዳዎችን የሚያገናኝ የአትበል ወንዝ ድልድይ እና  የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ተመርቀዋል።

በክልሉ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በዚህ አመት ለማጠናቀቅ ያቀዳቸውን 52 ፕሮጀክቶች አጠናቆ በዚሁ ሳምንት ለአገልግሎት ክፍት  በማድረግ ላ ይገኛል።

በዞኑ በጥቅሉ ከስድስት መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገልጿል ።

በሀይለየሱስ ስዩም

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.