Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጣሊያኑ አቻቸው ሉይጊ ዲማዮ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 16 ፣2012 (ኤፍ.ቢሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሉይጊ ዲማዮ ጋር ዛሬ በስልክ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ  በውይይታቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው እና ኮቪድ 19ን በጋራ መግታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከመስማማታቸውም ባለፈ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ መረጃ መለዋወጣቸው ተገልጿል።

አቶ ገዱ በዚሁ ወቅት  ጣሊያን የኢትዮጵያን ሪፎርም በመደገፍ እያደረገች ላለችው የልማት እርዳታ አመስግነው÷ በቀጣይም ኢትዮጵያ ከጣሊየን ጋር ያላትን ሀሉን አቀፍ ግንኙነትም ይበልጥ ለማጠናከር ትስራለች ብለዋል።

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በዓለም ላይ በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን የገለጹት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመከለተም ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከጣሊያን  መንግስት ጋር በትብብር መስራቷን እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።

አያይዘውም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ እና ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን እያደረጉት ያለውን ውይይት በተመለከተም  አቶ ገዱ ለጣሊያኑ አቻቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሉይጊ ዲማዮ በበኩላቸው÷ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥና ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመግታት ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራና የምታደርገውን የልማት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንበታ የሶስቱንም አገሮች ጥቅም ባማከለ መልኩ በውይይት እንዲፈታ ጣሊያን ታበረታታለችም  ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.