Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ እድገትን ለማስቀጠል በምታደርገው ጥረት ሩሲያ ያላትን ልምድ ለማካፈልና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያዎች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል፡፡

አምባሳደሩ በዚህ ወቅት÷ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ትግበራ የሚበረታታ ሥራ መስራቷን ከጉብኝቱ ተረድተናል ብለዋል፡፡

በተለይም ቴክኖሎጂና ዘመናዊነትን የእድገት መሠረት ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባላቸው ፍላጎት በርካታ ለውጦች በአጭር ጊዜ ውስጥ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን አጠናክራ ለማስቀጠል በምታደርገው ጥረት ሩሲያ ያላትን ልምድ ከማካፈል ጀምሮ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያን ልምድ ለመመልከት ወደ ኢንስቲትዩቱ የመጣው የዘርፉ ባለሞያዎች ልዑክ ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የቴክኖሎጂ ትብብር ለማጠናከር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር)÷በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን በሚመለከት ገለጻ ማድረጋቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.