የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዴቪድ ቢዝሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እና ለወደፊትም ሊሰራቸው ባሰባቸው እቅዶች ዙሪያ መክረዋል።