Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 775 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 848 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 184 ኢትዮጵያውያን፤ 1 ሰው የውጭ ዜጋ ሲሆኑ፥ የእድሜ ክልላቸውም ከ3 ወር እስከ 80 ዓመት የሆኑ 47 ወንዶች እና 138 ሴቶች ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (ከእነዚህም 105 ሰዎች ተመላሾችና በማቆያ የነበሩ)፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን፥ የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት የለም።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከሐረሪ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 1 ትግራይ ክልል) ማገገማቸውንም አስታውቀዋል።

ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 412 መድረሱንም ነው ዶክተር ሊያ ያስታወቁት።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ223 ሺህ 341 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 848 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 359 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 38 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 1 ሺህ 412 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ75 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.