Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ የግብርና ምርቶች ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ገበያውን ለማረጋጋት እየተከናወነ ባለው ሥራ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የተለያዩ የግብርና ምርቶች መግባታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በዚሁ መሠረትም 8 ሺህ 156 ኩንታል ጤፍ፣ 9 ሺህ 12 ኩንታል ገብስ፣ 7 ሺህ 522 ኩንታል በቆሎ፣ 38 ሺህ 844 ኩንታል ሽንኩርት እና 17 ሺህ 476 ኩንታል ቲማቲም ከኦሮሚያ ክልል በትስስር ወደ አዲስ አበባ ገብቷል ብለዋል፡፡

የሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና ገበያ ማረጋጋት ሥራው በአንዳንድ ምርቶች ዋጋ ላይ ቅናሽ በማሳየት ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.