Fana: At a Speed of Life!

በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ በንቃት መሳተፍ የኅልውና ጉዳይ ነው – ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የተጎዱ ሥነ-ምኅዳሮችን መልሶ በማልማት የአካባቢ ደኅንነትን ለመጠበቅ ሚናው የጎላ በመሆኑ ሕዝቡ በንቃት እንዲሳተፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ የዝግጅት ሥራዎች ተጠናቅቀዋል፡፡

የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላውን አስመልክቶ አቶ ጥላሁን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭነትን በዘላቂነት ለመግታት የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

የተጎዱ ሥነ-ምኅዳሮችን መልሶ በማልማት የአካባቢ ደኅንነትን ለመጠበቅ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመግራት የአረንጓዴ ዐሻራ ሚና ከፍተኛ  መሆኑን በመገንዘብ ሕዝቡ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ነገ ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ በየአካባቢው በተዘጋጁ የተከላ ቦታዎች በመገኘት እስከ ምሽቱ 12 ሠዓት በከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት ሕዝቡ በንቃት በመሳተፍ ዐሻራውን እንዲያኖር ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.