Fana: At a Speed of Life!

ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ በረራዎች በከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች ተዛወሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ በረራዎች በከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች መዛወራቸውን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ÷ ዛሬ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት አብዛኛዎቹ በረራዎች በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም ፡፡

ይህን ተከትሎም አብዛኛዎቹ በረራዎች አቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች ተመልሰው እንዲያርፉ መደረጉን ነው የገለጸው፡፡

የተከሰተው የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩም ተመላክቷል፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎች የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በመዲናዋ በተፈጠረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በመንገደኞች ላይ ለደረሰው መጉላላትም አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.