በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 234 ሚሊየን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር እስካሁን 234 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 234 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ በ8 ሺህ 454 የችግኝ ጣቢያዎች 11 ሚሊየን ዜጎች መሳተፋቸውን ነው የገለጹት፡፡
በዚህም በእስካሁኑ ሒደት 93 ሺህ ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈን መቻሉን ሚኒስትር ዴዔታዋ ተናግረዋል፡፡