Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ከአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የአፍሪካ የቴክኒክ ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የአፍሪካ የቴክኒክ ትብብር ክፍል ዳይሬክተር ሹካት አብዱልራዛቅ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአቶሚክ ቴክኖሎጂ ዙሪያ በጋራ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ መክረዋል።

የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በኒውክሌር መስክ የሚሰራ ሲሆን፥ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰላማዊ አጠቃቀምን ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚሰራ ተቋም ነው።

ኢትዮጵያ በኦስትሪያ ቪዬና በተካሄደው 63ኛው ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ አመታዊ ጉባኤ ላይ “የተጨማሪ ፕሮቶኮል” መፈረሟን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.