ቢዝነስ

በተቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ መሰረት ግብይት በማይፈጽሙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

June 24, 2020

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸውን አስታውሷል፡፡