Fana: At a Speed of Life!

የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪውን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ እንዳሉት÷ የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የጎላ ሚና እያበረከተ ይገኛል፡፡

በዚህ ረገድ በኤርፖርት ደረጃ ተግባራዊ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ሳይሸራረፉ ለመተግበር የዘርፉ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በአቪዬሽን ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ልቆ ለመገኘት በኤርፖርት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ጥራት ያላቸው እና ደንበኛ ተኮር መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣኑ የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካትና ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን መልካም ስም ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ አንደሆነ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.