Fana: At a Speed of Life!

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የታማኝነትና የቅንነት እሴቶችን ሊላበሱ ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፐብሊክ ሰርቪስ ቀንን በማስመልከት በመንግስታቱ ድርጅት አዘጋጅነት በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል

በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግርም የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ተቋማትን ለመገንባት ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ሚናቸውም ከፖለቲካዊ ልዩነት በላይ የሚሻገርና የሀገርን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም የታማኝነትንና የቅንነት እሴቶችን ሊላበሱ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ቀን ሲታሰብ ዓለም ከፍተኛ ቀውስ በገጠማት በዚህ ወቅት በሰዎች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ለሚገኙ የህዝብ አገልጋዮች ክብር በመስጠት ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

መላውን የስራ ዘመናቸውን በሀገር ውስጥና በውጭ በተለያዩ ሃላፊነቶች በማገልገል ማሳለፋቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ ይህንን ከማድረግ የበለጠ የሚያኮራ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡

መረጃው የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ነው

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.