ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀውን መድረክ አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሲዳማ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ አስጀምሯል፡፡
በመድረኩ 1 ሺህ 800 የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡
ለ7 ቀናት የሚካሄደው መድረኩ÷ሀገራዊ መግባባት የሚፈጥሩ አጀንዳዎች በህዝባዊ ውይይት የሚሰበስቡበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በፍቅርተ ከበደ