Fana: At a Speed of Life!

በፀሐይ የሚሠሩ የውኃ መሳቢያዎች ውኃ ለማቅረብ አይነተኛ መሳሪያ መሆናቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የውኃ መሳቢያዎች (ፓምፖች) ለዝናብ አጠር አካባቢዎች ለመጠጥም ሆነ ለግብርና ሥራ የሚሆን ውኃ ለማቅረብ ሁነኛ መሳሪያ መሆናቸው ተመላከተ፡፡

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በኮትዲቯር አቢጃን እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ዓለም አቀፉ የሶላር አሊያንስ በአዘጋጀው እና በጸሐይ ኃይል ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይም÷ ሚኒስትሩ በጸሐይ ኃይል ልማት ዙሪያ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን አቅርበዋል፡፡

በተለይም በዓለም አቀፉ የሶላር አሊያንስ ድጋፍ በኢትዮጵያ እየተተገበሩ የሚገኙ የጸሐይ ኃይል ልማት ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡

በዚህም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በይርጋ ጨፌ ወረዳ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የሶላር ፓምፕ ፕሮጀክት በአፍሪካ ደረጃ በተሞክሮነት መቅረቡን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከስብሰባው ጎን ለጎን ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የሶላር አሊያንስ ዋና ዳይሬክተር አጃይ ማቱር (ዶ/ር) ጋር ትብብሮችን በይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ለይ መክረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.