በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 323 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 323 ደረሰ፡፡
በከተማዋ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 147 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 65 የከተማዋ ነዋሪዎች፣ 1 የውጪ ዜጋ ሲሆን 81 ሰዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ የስደት ተመልሾች ናቸው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 63 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን ከአዲስ አበባ ፐሬስ ሴክሪታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።