አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ዝላታን ሚሌሲክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል በሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አነስተኛ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶችን በዘላቂነት ለማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡