ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል አለም አቀፍ የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል አለም አቀፍ የበይነ መረብ ዘመቻ በኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች እና የኢትጵያ ወዳጆች ሊካሄድ ነው።
አለም አቀፍ ዘመቻው የተባበሩት ኢትዮጵያዊያን ለሰላምና እርቅ የተሰኘው ድርጅት ከዓለም አቀፉ የእውቀት ልውውጥ ኔትወርክ ጋር በተመባበር የሚያዘጋጁት ነው።
የዘመቻው ዓለማ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለህዳሴ ግድብ እና የድርድር ሂደት ግንዛቤን ለመፍጠር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
እንዲሁም የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ ገቢ ለማሰብሰብ የሚያስችል ዘመቻ መሆኑ ተጠቁሟል።