በምስራቅ ቦረና ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን ሊበን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከአዶላ ዋዩ ወደ ነጌሌ ቦረና ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ከሲኖትራክ ጋር ተጋጭቶ መከሰቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ትራፊክ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር በላቸው ቲኬ ተናግረዋል፡፡
በተፈጠረው አደጋም የዶልፊኑን ሹፌር እና ረዳት ጨምሮ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነው ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመው÷አሽከርካሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ በጥንቃቄ ማሽከርከር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡