በክልሉ የ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) የምዝገባ መርሐ-ግብሩን በኢሉአባቦር ዞን በቾ ወረዳና መቱ ከተማ ያስጀመሩ ሲሆን÷ ምዝገባው እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን ከ12 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁም ተመላክቷል፡፡