ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ በአንድ ቀን ከ35 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ

By Meseret Demissu

June 25, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 35 ሺህ 900 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማስመዝገቧን ጆንስ ሆፒኪንስ ዩኒቨርስቲ አስታውቋል።

ከዚያም ባለፈ በሀገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት 756 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በምጣኔ ሀብት ዓለምን በምትመራው አሜሪካ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ካሏት 50 ግዛቶች ግማሽ በሚሆኑት በየቀኑ የበሽታው ስርጭት በመጨመር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የተጠጋ ሲሆን÷ የሟቾች ሰዎች ቁጥርም ከ121 ሺህ በላይ አሻቅቧል ፡፡

ምንጭ፦ዴይሊ ኔሽን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።