Fana: At a Speed of Life!

ወርልድ ቪዥን-ኢትዮጵያ ለሚኒስቴሩ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ወርልድ ቪዥን-ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።

በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ፍቃዱ ያደታ ÷ ወርልድ ቪዥን -ኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 መከላከያ እና መቆጣጠሪያ የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ድጋፎቹ ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሀገር አቀፍ ርብርብ ያግዛልም ነው ያሉት ፡፡

አቶ ፍቃዱ ለተደረገዉም ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዉ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የወርልድ ቪዝን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢድዋርድ ብራውን በበኩላቸው÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ስራዎችን ለማገዝ የሚረዳ የሙቀት መለኪያ ፣ ግሎቭ ፣ ማስክ እንዲሁም የኮቪድ-19 ህክምና የሚዉሉ ቁሳቁሶችን መለገሳቸዉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ወረርሽኙን ለመከላከል የሚረዱ ድጋፎች ማድረጋቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባር ለማገዝ አስፈላጊውን ድጋፍ በቀጣይም እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.