Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 1ኛ ዓመት ምስረታ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት 1ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “ከአዲስ ምዕራፍ በወል እሴት ወደ መስፈንጠር ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

 በአከባበሩ ላይም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ በፓናል ውይይትና ሌሎች መርሐ-ግብሮች የሚከበር ሲሆን÷ የተዘጋጁ ሠነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ተመላክቷል።

ከክልሉ ምስረታ ጀምሮ የተካሄዱ የልማትና መልካም አሥተዳደር ሥራዎችን የሚመለከት የፎቶ ዐውደ-ርዕይ መከፈቱንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.