በሲዳማ ክልል የተገኙ ስኬቶችን በማሰብ ”የመሻገር ቀን” እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን በማሰብ ጳጉሜን 1 ”የመሻገር ቀን” እየተከበረ ነው፡፡
ዕለቱ እየተከበረ የሚገኘው “የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ ቡድንም በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ድሎችን ማስመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም እነዚሁ ስኬቶች እየተጎበኙ ነው፡፡