አንዲት እናት በሕግ ሲፈለግ የነበረ ልጃቸውን ለፖሊስ አሳልፈው ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ እናት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በሕግ ሲፈለግ የነበረ ልጃቸውን ለፖሊስ አሳልፈው ሰጡ፡፡
ግለሰቡ በወረዳው አይበራ ሳንቃ ቀበሌ በሚገኝ ጫካ በመግባት የተለየዩ ወንጀሎችን በመፈጸም ድርጊት መጠርጠሩን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አዳነ ዓለማየሁ ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ እንዳመላከተው÷ ጫካ ውስጥ በመሆን በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፎ የተጠረጠረው ምሥራቅ አበበ በወላጅ እናቱ አማካኝነት ለፖሊስ እጅ ሰጥቷል፡፡
የግለሰቧን ተግባር ያደነቀው ፖሊስ÷ ወንጀልን በጋራ ለመከላከል እንዲቻል ሕብረተሰቡ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጎን በመቆም የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርቧል፡፡