የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሸጋገር ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሸጋገር በየዘርፉ ያለን አካላት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ሴት የሠራዊት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል አባል በመሆናችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ብለዋል።
የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሴቶች ድርሻ ወሳኝነት አለው ያሉት ሚኒስትሯ÷ ሴትነታችን ሳይበግረን ከአሰብነው የስኬት ጫፍ ለመድረስ ራዕይ ሊኖረን ይገባል ነው ያሉት፡፡
የራሳቸውን የስኬት መነሻና የሕይወት ተሞክሮም ማጋራታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሸጋገር በየዘርፉ ያለን አካላት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡