ስፓርት

ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ

By Tibebu Kebede

June 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡

የአንፊልዱ ክለብ ትናንት ምሽት ተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በቼልሲ መሸነፉን ተከትሎ ከ30 አመት በኋላ ሻምፒዮንነቱን አውጇል፡፡

የክለቡ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ከረጅም አመታት በኋላ የተገኘውን ድል አክብረውታል፡፡

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ከደጋፊዎች ጋር ድሉን ስለማክበር እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡

ትናንት ምሽት በተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በርንሌይ ዋትፎርድን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አርሰናል ከሜዳው ውጭ ሳውዝሃምፕተንን 2 ለ 0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡

በምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ደግሞ ቼልሲ ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በቀጣዩ አመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማሳካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡