Fana: At a Speed of Life!

ድርጅቱ ከቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ከቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመጀመሪያው የቻይና ምሥራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የሕግ ማስከበር እና ደኅንነት ምክክር መካሄዱን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በምክክሩም 14 የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊስ ተቋማት እና የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል፣ በኦፕሬሽንና በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

ትብብሩ በቻይና እና በቀጣናው ያለውን የፀጥታና ደኅንነት ሥራዎች የበለጠ የሚያጠናክር ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.