Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪን መገለጫዎች በመጠበቅ ውጤታማ ሥራዎች እንሠራለን- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መገለጫ የሆኑ እሴቶችን በይበልጥ በማጎልበት በቅንጅት ውጤታማ ሥራዎችን እንሠራለን ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

በክልሉ ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን “ኀብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉ ሕዝብ እና የተለያየ ሐይማኖት ተከታዮች በመከባበር እና በመደጋገፍ እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

ይህን ጨምሮ የክልሉ መገለጫ የሆኑ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻል እና የአብሮነት እሴቶች ሳይሸራረፉ እንዲቀጥሉ በትኩረት እንሠራለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሕግን የማስከበር፣ የዜጎችን የልማትና የመልካም አሥተዳደር ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራዎች ላይም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.