Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል በተጠናቀቀው ዓመት ስኬታማ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በርካታ ተግባራትን በስኬት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

የአየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ አየር ኃይል የድል ዓመት ነበር ብለዋል፡፡

በአዲሱ ዓመትም የኢትዮጵያ አየር ኃይል በላቀ የወትሮ ዝግጁነት አቅም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና ተባባሪ የውስጥ ባንዳዎች ፍላጎታቸው መቼም እንደማይሳካ ተረድተው ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.