Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዓመት አዳዲስ ውጤቶችን እውን ለማድረግ የምንተጋበት ነው- አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ዓመት ፀጋዎቻችንን አስተባብረን በማንቀሳቀስ አዳዲስ ውጤቶችን እውን ለማድረግ የምንተጋበት ዓመት ነው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ አዲሱ ዓመት አቅሞቻችንን እና ፀጋዎቻችንን አስተባብረን በማንቀሳቀስ አዳዲስ ውጤቶችን እውን ለማድረግ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነውና የክልሉ ሕዝቦች የየበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የርዕሰ መሥተዳድሩ የመልካም ምኞት መግለጫ ሙሉ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል፡-

ለ2017 አዲስ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ!

ለአዲሱ ዓመት ለ2017 ዓመተ ምህረት፣ የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሰን! አደረሳችሁ! እያልኩ ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን መልካም ምኞቴን በአክብሮት እገልፃለሁ።

ወደ አዲሱ ዓመት ስንሸጋገር አዲስ ተስፋ ሰንቀን፣ አዳዲስ ዕቅዶችን ይዘን ፣ለአዳዲስ ዉጤቶች ለመብቃት ብርታታችንን፣ ፅናታችንን ፣ ትጋታችንን ከፍ በማድረግ ነዉ።

መላዉ የክልላችን ሕዝቦች!

አዲሱ ዓመት አቅሞቻችንን እና ፀጋዎቻችንን አስተባብረን በማንቀሳቀስ አዳዲስ ዉጤቶችን እዉን ለማድረግ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነዉና መላዉ የክልሉ ሕዝቦች የየበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አዲሱ ዓመት በክልላችን/ በሀገራችን በሁሉም መስኮች እመርታ የምናሳይበት፣ በሀሳብና በተግባር ተዋህደን ጠንካራ አንድነት በመፍጠር አዳዲስ ስኬቶችን የምናስመዘግብበት እንዲሆን እመኛለሁ ።

አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የአብሮነት፣ የስኬትና የሐሴት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.