የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከጤና ዘርፍ ጋር አስተሳስሮ ለመሥራት ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከጤና ዘርፍ ጋር አስተሳስሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው በጤና ሚኒስቴር እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከፍተኛ አመራሮች መካከል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ዛሬ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ከጉብኝታቸው ጎን ለጎንም ለፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ማድረጋቸውን የፕሮግራሙ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ወቅትም ከፕሮግራሙ አመራሮች ጋር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከጤና ዘርፍ ጋር ስለሚኖረው ትሥሥር እና በቀጣይ ስለሚደረጉ የጋራ አቅጣጫዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል፡፡