የሀገር ውስጥ ዜና

የሕክምና ግብዓቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ገለፁ

By Feven Bishaw

June 26, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለሟሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገለፁ።

የጤና ሚኒስትሯ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ለጤና ተቋማቱ በግዥ አልያም በዕርዳታ የሚገኙ የሕክምና መሳሪያዎችና ግብዓቶችን የማሰባሰብ ሥራው ተጠናክሯል ብለዋል።